ሲጂን የልዩ ሀይል ካፕቴን ሲሆን ከጓደኛው ዴ-ዩንግ ጋር ሆኖ ሊይዘው የነበረ አንድ ሌባ ጉዳት ይደርስበት እና ሆስፒታል ይገባል:: ሲጂን ሌባውን ፍለጋ ሆስፒታል ይሄዳል፡ እዛም ዶክተር ካንግ ሞዩንን ይተዋወቃል፡ ወዲያም በፍቅር ይወድቃል፡ ወታደሩ ሲጂን እና ዶክተሯ ሞዩን ግንኙነት ይጀምራሉ፡ ሆኖም ግን ብዙም ሳይቆዩ ሲጂን ለሰላም ማስከበር ወደ ሩቅ ሀገር ይላካል፡ ከስምንት ወራት በኋላ በሚገርም የህይወት አጋጣሚ ዶክተሯ እና ወታደሩ በባእድ ሀገር ይገናኛሉ፡፡