"የፍቅር ነገር” የሲይላን ታሪክ ነው፡፡ ማለቂያ የለሽ የህይወት ውጣውረዶችን ያሳለፈው የኮርኩት ህይወት ውስጥ ደስታና ተስፋን ይዛለት መጥታለች፡፡ ኮርኩት ወጣትና መልከመልካም ወጣት ሲሆን ጀርመን ውስጥ ጥሩ የሚባል ህይወትን ሲመራ ቆይቷል፡፡በልጅነቱ በወላጆቹ ከተተወ በኋላ በማደጎ ቢያድግም ከአሳዳጊዎቹም እንደገና የመለያየት እጣ ደርሶታል፡፡ ሴይሊን ኑሮዋን በኢስታምቡል ያደረገች ውብ ወጣት ስትሆን በሞያዋም ለዝነኛው ድምጻዊ ቶልጋ የፋሽን ዲዛይነር በመሆን ትሰራለች፡፡ቶልጋ ለሴይሊን የፍቅር ጥያቄ ቢያቀርብም እሷ ግን ለሱ ተመሳሳይ ስሜት አልነበራትም፡፡ሲይላን እና ኮርኩት ጀርመን በተገናኙ ጊዜ የሁለትም ህይወትና እጣፈንታ ተቀየረ፡፡