ሽምጥ ተዋጊዎች ሚሊዳን በምግብ አማልለው ሲወስድዋት ዘጠኝ አመቷ ብቻ ነበር፡፡ ለሚቀጥሉት ሰባት አመታት በተዋጊዎቹ ተይዛ በግድ ህፃን ተዋጊ ትሆናለች፡፡
ቤተሰቦቿ በጦርነት የሞተች ይመስላቸዋል፡፡ከዛም በድንገት ሜሊዳ ወደ መጣችበት ከተማ በአስራ ስድስት አመቷ ሽጉጥ እና ቦምብ ይዛ ትመለሳለች፡፡ ወንድ አያቷ ብቻ ነው ጉንጯ ላይ ባላት ምልክት ለይቶ የሚያውቃት፡፡
ከዛም በነጋታው የመከላከያ ሃይሎች የውለታ ገንዘቡን ፈልጎ በጠራቸው ጠቋሚ ተጠርተው ቤቷን ይወሩታል፡፡
‹የገዛ አባቴ አሳልፎ እንደሰጠኝ አውቃለሁ፡፡› ብላ ታስታውሳለች፡፡