የቃና ሳተላይት እና ፍሪክዌንሲ
Eutelsat 8 West B
ሞገድ: 11512
ድረ ገጽvs ድህረ ገጽ: አቀባዊ
ሲምቦል ሬት: 27500
FEC: 7/8

ሚያዝያ 10/2013
 

የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ

ቃና ቲቪ እና ይህ ድረ-ገፅ የሞቢ ግሩፕ አካል በሆነው በቃና ኢንተርቴይንመንት ሊሚትድ ባለቤትነት የሚተዳደሩ ናቸው፡፡

በድረ-ገፃችን በሚኖርዎት ቆይታ የግል መረጃ ደህንነትዎን ለማረጋጥ እንተጋለን፡፡ ስለእርሶ የምናገኘውን መረጃ እርስዎ ድረ-ገፃችንን

ሲጎበኙ የሚፈልጉትን አይነት አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችለን የምንጠቀምበት ይሆናል፡፡ ለእኛ የሚሰጧቸው የግል መረጃዎች

ለሌሎች አለአግባብ እንዲሰራጩ የማይፈልጉ መሆንዎን እያከበርን፤ ከዚህ ቀጥሎ የግል መረጃ እንዴት እንደምንሰበስብ፣ ለምን

እንደምንጠቀምበት እና እርሶ የሚሰጧቸውን መረጃዎች በምን መልኩ መቆጣጠር እንደሚችሉ እንገልፃለን፡፡

የተዘረዘሩትን የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ ማንበብና መረዳት የእርስዎ ሃላፊነት ነው፡፡ ይህን ፖሊሲ ለመረዳት ካልቻሉ ወይም

ለመቀበል ፈቃደኛ ካልሆኑ የድርጅታችን የመረጃ ጥበቃ ሰራተኛን ከታች በተቀመጠው አድራሻ በመጠቀም ማናገር ይችላሉ፡፡ በዚህ

የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ ሙሉ ለሙሉ የማይስማሙ ከሆነ እና በዚህ ፖሊሲ ለመተዳደር ፈቃደኛ ካልሆኑ ድረ-ገፁን ለመጠቀም

የሚያስችል ፈቃድ አያገኙም፡፡

 

  1. የምንሰበስባቸው መረጃዎች

የግል ፍላጎትዎን የሚመጥን አገልግሎት ለመስጠት ስንል የድረ-ገፃችን ተጠቃሚ ለመሆን ምዝገባ ሲያደርጉ ወይም በሌላ

በማንኛውም ጊዜ የግል መረጃዎችን እዲሰጡን ልንጠይቅዎት እንችላለን፡፡ በተጨማሪም የኛን የስራ ውጤቶች ለማዘዝ ሲፈልጉ ወይም በድረ-ገፃችን ላይ ከሚካሄዱት ውይይቶች በአንዱ ለመሳተፍ ሲፈልጉ ወይም የድረ-ገፃችን ማህበረሰብ አካል ለመሆን ሲፈልጉ የግል

መረጃዎን ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡ በነዚህ ገፆች ላይ የምንሰበስባቸው መረጃዎች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፡- ስምዎን፣ ኢሜል

አድራሻዎን፣ የፖስታ ሳጥን ቁጥሮን፣ የሞባይል/ የቤት ስልክ ቁጥሮን፣ ፆታዎን እና የልደት ቀንዎን ያጠቃልላል፡፡ እንዲሁም ሌሎች

ተጨማሪ መረጃዎች ለምሳሌ ዝንባሌዎን፣ አስተያየትዎን እንዲሁም ከላይ የገለጽናቸውን አላማዎቻችንን ለማገዝ እንዲረዳን እና

የደንበኞቻችን ልምዶች እና አካሄዶችን የበለጠ ለመረዳት እንዲያስችለን አገልግሎቶቻችንን እንዴት እንደሚጠቀሙ

እንዳስፈላጊነቱ ልንጠይቅዎ እንችላለን፡፡

የግል መረጃዎችዎን ለመስጠት የማይገደዱ ቢሆንም መረጃዎችን ለመስጠት ፈቃደኛ ካልሆኑ አንዳንድ አገልግሎቶቻችንን ለእርስዎ

ለማቅረብ ላንችል እንችላለን፡፡

2. የሚሰጡንን መረጃዎች እንዴት እንጠቀማቸዋለን?

የሚሰጡንን መረጃዎች የምንጠቀማቸው፡-

- ድረ ገፁን፣ አገልግሎታችንን እና የእርሶን ቆይታ ለመከታተልእና ለማሻሻል፣

- ለእርስዎ በግል የምንሰጥዎትን አገልግሎቶች ለማጠናከር እና ለመቆጣጠር (ማለትም ዜናዎችን እና ቃና ቲቪን እና ሌሎች ከድረ-

ገፆቻችን ወይም አገልግሎቶቻችን ጋር ተዛማጅ የሆኑ መረጃዎችን በኢሜል፣ በፖስታ፣ በፋክስ ወይም ስልክ ለማሰራጨት ወይም

አንድ የተወሰነ አገልግሎታችን በጥገና ምክንያት መቁረጡን ለማሳወቅ፣

- ማንኛውም እርስዎን አስመልክቶ የተነሱ ቅሬታዎችን እና ጥያቄዎችን ለማስተናገድ እና ለመመለስ፣

- ድረ-ገፁ ላይ ያስገቡትን መረጃ እንዲሁም የሰጡንን የተለያየ አይነት ይዘት ያላቸው ስራዎችን በተመለከተ ከእርስዎ ጋር

ለመገናኘት እና፣

- የደንበኞችን ልምድ እና አካሄድ ለመረዳት፣

3. እርስዎን በግል የምናናግርባቸው ሁኔታዎች፣

በሚከተሉት ሁኔታዎች እርስዎን በግል ልናናግር እንችላለን፡

- እርሶ ከተመዘገቡባቸው እና በስራ ላይ ካሉ አገልግሎቶቻችን ጋር በተገናኘ የጠየቋቸውን አገልግሎቶች ለማድረስ የምንችል

መሆኑን ለማረጋገጥ፣

- በቀጣይ ሌሎች መልእክቶች እዲደርስዎ የጠየቁ እንደሆነ፣

- ድረ-ገፁ ላይ ካደረጉት አስተዋጽኦ ጋር በተገናኘ(ለምሳሌ ከማንኛውም አይነት ጦማሮች፣ የመልእክት ሳጥኖች ወይም

በድረ-ገፁ ላይ የተዘጋጁ ውይይቶች ጋር በተገናኘ)፣

- ስለአገልግሎቶቻችን በሚደረጉ ጥናቶች እንዲሳተፉ ለመጋበዝ (መሳተፍ ምን ጊዜም በእርስዎ ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ

ነው፡፡)

- እንዲሁም ለገበያ ጥናት አላማዎች በግልፅ ለመሳተፍ የተስማሙ እንደሆነ፣

ሌሎች የውስጥ ገፆች የተወሰኑ አገልግሎቶችን አስመልክቶ እርስዎን ለማነጋገር ስለምንወስዳቸው እርምጃዎች መረጃ ይሰጥዎታል፡፡

4. የገበያ ጥናትን አስመልክቶ ከእኔ ጋር የሚኖረው ግንኙነት ምን ይመስላል?

በማንኛውም ጊዜ እና በማንኛውም ቦታ በእርሶ ጥያቄ መሰረት ብቻ፡

- ኢሜል በመላክ፣ በስልክ (አጭር የፅሁፍ መልእክትን ጨምሮ) ወይም በፖስታ መልእክት ስለነባር እና አዳዲስ

አገልግሎቶቻችን፣ ምርቶቻችንን እንዲሁም ሌሎች ልዩ እድሎችን አስመልክቶ መረጃዎችን ለመላክ እና ወቅታዊ መረጃ

ለመላክ፤

- እርስዎን ይመለከታሉ ብለን ያልናቸውን የተመረጡ የሶስተኛ ወገን ምርቶችን እና አገልግሎቶችን የሚመለከቱ ነገሮችን

በኢሜል፣ በስልክ ወይም በፖስታ ለመላክ(በማንኛውም ጊዜ እኛን በማናገር የሰጡትን መረጃ የማስወገድ እድሉ አለዎት፡፡)

እርስዎን በማንኛውም መልኩ እንዳናናግርዎት ወይም እርስዎ የሰጡንን መረጃዎች ለሌላ ሶስተኛ ወገን እንዳንናገር

በመጀመሪያ ምዝገባ ሲያደርጉ ወይም በኋላ በግል መረጃዎችዎ ላይ በሚያደርጓቸው ማስተካከያዎች እና ማሻሻያዎች

ለመከልከል ይችላሉ፡፡ ሆኖም አልፎ አልፎ እርስዎ ይወዷቸዋል ብለን ያሰብናቸውን ምርቶች እና አገልግሎቶች አስመልክቶ

ልናናግርዎ እንችላለን፡፡ ይህ ከእኛ (ወይም ከወኪሎቻችን) ብቻ የሚላክልዎ ሲሆን ይኸውም እነዚህን አይነት መልእክቶች

መላካችንን የማይቃወሙ የሆነ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡

5. የግል መረጃዎትን ለሶስተኛ ወገን እንናጋራለን?

መረጃዎችን ለመስጠት ካልተገደድን ወይም በህግ የተፈቀደልን ካልሆነ በስተቀር (ማለትም ለምሳሌ ለመንግስት አካላት እና

ለህግ አስፈፃሚ ተቋማት/ወይም በዚህ ስምምነት ውስጥ በሌላ ቦታ እደተገለፀው ካልሆነ በስተቀር በአጠቃላይ የእርስዎን

የግል መረጃ በሞቢ ግሩፕ ውስጥ ወይም አጋር ድርጅቶች ውስጥ ብቻ የምንጠቀምበት ይሆናል፡፡

6. ድረ-ገጹ ላይ የሚጫን አስጸያፊ ወይም ተገቢ ያልሆነ ይዘት

ድረ-ገጹ ላይ ወይም ሌላ ማንኛውም ቦታ ላይ አስጸያፊ፣ ተገቢ ያልሆነ ወይም ተቃውሞ ሊገጥመው የሚችል ነገር ከጫኑ ወይም

ከላኩ ወይም ደግሞ በድረ-ገፁ ላይ በማንኛውም አይነት መንገድ ተገቢ ያልሆነ ተግባር ካሳዩ እነዚህን ተገቢ ያልሆኑ ባህሪያት

ለማስቆም የእርስዎን የግል መረጃ ልንጠቀም እንችላለን፡፡ ተግባራዊ የሚሆኑ ሕጎችን (ለምሳሌ የጫኑት መረጃ የሌላን ወገን ስም

የሚያጠፋ ከሆነ ወዘተ) የግል መረጃዎን ተጠቅመን ለቀጣሪዎ፤ የትምህርት ቤት ኢሜይል/ኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪ ለሆነው

ወይም የሕግ ጠባቂ አካላት ስለ ይዘቱና ስለ እርስዎ ድርጊት ልናሳውቅ እንችላለን፡፡ ነገር ግን አንዳድ ጊዜ ሌሎች ሶስተኛ ወገኖች

መረጃዎችን እንዲያጠናቅሩ ልናደርግ የምንችልባቸው ሁኔታዎች ይኖራሉ፡፡ እነዚህም ሶስተኛ ወገኖች የድርጅታችንን መመሪያዎች

በሙሉ በሚገባ አክብረው እንዲሰሩ የምናስገድዳቸው ሲሆን የእርስዎን የግል መረጃ ለራሳቸው የንግድ እንቅስቃሴ

እንዳያውሏቸውም ጭምር እናስገድዳን፡፡

7. ዕድሜዬ 16 እና ከዚያ በታች የሆነ ተጠቃሚ ከሆንኩስ?

ዕድሜዎት 16 እና ከዚያ በታች ከሆነ በድረ-ገፁ የግል መረጃዎን በሚሞሉበት በማንኛውም ጊዜ ከመሙላትዎ በፊት

የወላጅ/የአሳዳጊዎን ፈቃድ ይጠይቁ፡፡ በዚህ የማይስማሙ ተጠቃሚዎች የግል መረጃዎቻቸውን እንዲሰጡን አንፈቅድም፡፡

ዕድሜዎ ከ16 ዓመት በታች ሆኖ ያለ ወላጅ/አሳዳጊ ፈቃድ የግል መረጃዎን ለመስጠት እየሞከሩ/ የሰጡ መሆኑን ከደረስንበት

የሰጡትን መረጃ የማንቀበል ከመሆኑም በላይ የሰጡትን መረጃ ከማህደሮቻችን ለማስወገድ እርምጃዎችን የምንወስድ ይሆናል፡፡

ይሄም መረጃዎት ውስጥ ገብተን ዕድሜዎንና ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን እንድናረጋግጥ ሊያስገድደን ይችላል፡፡

8. የተጠያቂነት ወሰን

ይሄ ድረ-ገጽ ከእኛ የተለየ አሠራር ወዳላቸው ሌሎች ድረ ገጾች የሚወስዱ መጠቁሞች ሊኖሩት ይችላል፡፡ ለምሳሌ አንድ መጠቁም

ላይ ሲጫኑ ከኛ ድረ-ገፅ ሊያወጣዎ ይችላል፡፡ በእነኚህ ሶስተኛ ወገን ድረ-ገጾች በሚሰጥ መረጃ ላይ ምንም ዓይነት ባለቤትነትም ሆነ

ኃላፊነት የሌለብን በመሆኑ የሌላኛውን ድረ-ገጽ የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ ማንበብ ይኖርብዎታል፡፡

አልፎ አልፎ በሚታወቁ ሶስተኛ ወገኖች ስፖንሰር የተደረጉ ወይም በጋራ በመሆን የሚቀርቡ ይዘቶችን (ለምሳሌ ውድድሮችና

ማስታወቂያዎችን) ልናሰራጭ እንችላለን፡፡ ይህም ከሶስተኛ ወገን ጋር ያለን ግንኙነት እርስዎ በድረ-ገጹ ውስጥ ተሳትፎ ለማድረግ

በፈቃደኝነት የሰጡትን የግል መረጃ ሶስተኛ ወገኖችን ለማየት ያስችላቸዋል፡፡ ሆኖም እነኚህ ሶስተኛ ወገኖች በነዚህ መረጃዎች ላይ

የሚኖራቸውን አጠቃቀም ልንቆጣጠር የማንችል በመሆኑ ለነሱ አጠቃቀም ተጠያቂ አይደለንም፡፡ በነዚህ ሶስተኛ ወገኖች ላይም

ቁጥጥር ለማድግ አንችልም፡፡ ነገር ግን የግል መረጃዎን ለሦስተኛ ወገን የምንሰጥ ከሆነ ጥያቄው ልክ እንደቀረበልን ለእርስዎ

የምናሳውቅዎት ይሆናል፡፡

ድረ-ገጹ ላይ የሚያዩዋቸውን ማስታወቂያዎች ለማዘጋጀት ወይም ለማቅረብ የታወቁ ሶስተኛ ወገኖችን ልንጠቀም እንችላለን፡፡ ሆኖም

ይሄ የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ የሶስተኛ ወገን ማስታወቂያ አቅራቢ ከእርስዎ የሚወስደውን መረጃ የሚያስተዳድር ወይም የሚገዛ

አይደለም፡፡

9. ተጠያቂ የማንሆንባቸው ሁኔታዎች

በቀጥታ ቁጥጥር ከምናደርግባቸው ሁኔታዎች ውጭ በምንም ዓይነት መንገድ ሃላፊም ሆነ ተጠያቂ አይደለንም፡፡ ውስብስብና ዘወትር

ተለዋዋጭ ባህሪ ባለው ቴክኖሎጂያችንና ስራችን ምክንያት፣ አሠራራችን ከስህተት የጸዳ ለመሆኑ ዋስትና አንሰጥም፡፡ የግል መረጃዎን

አጠቃቀም ወይም መለቀቅ ጋር በተገናኘ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ፣ በአጋጣሚም ሆነ በምክንያት ወይም በቅጣት መልኩ

ለሚደርስብዎ ኪሳራ ሕግ እስከፈቀደ ድረስ ተጠያቂ አይደለንም፡፡

10.የግል መረጃዎን ለምን ያክል ጊዜ እናስቀምጠዋለን?

የግል መረጃዎን ለሚመለከተው አገልግሎት አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ የምናቆየው ይሆናል፡፡ ለድረ-ገፁ አስተዋፅኦ ያደረጉ እደሆነ

የሰጡትን መረጃ የምናቆየው መረጃውን ለተቀበልንበት ጉዳይ (ጉዳዮች) አስፈላጊ አስከሆነ ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡

11. ምን ዓይነት የግል መረጃዎቼን እንደምታስቀምጡ ለማወቅ እችላለሁ?

በእንግሊዝ የመረጃ ጥበቃ አዋጅ (1998) መሠረት ስለ እርስዎ የምናስቀምጠውን የግል መረጃዎትን ቅጂ የማግኘትና ስህተቶች

እንዲስተካከሉ የመጠየቅ መብት አለዎት፡፡ ለመረጃ ጥያቄ 10 ዶላር የምናስከፍል ሲሆን በሁለት የተረጋገጡ ፎቶዎች ማንነትዎን

እንዲያረጋግጡልን እንጠይቅዎታለን፡፡ የእርስዎን የግል መረጃዎች ለማቅረብ፣ ለማስተካከልና ለመሰረዝ የሚቻለውን ያክል ጥረት

እናደርጋለን፡፡

እባክዎ ይሄን የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲን አስመልክቶ ያለዎትን ጥያቄ እና አስተያየት ለመረጃ ጥበቃ ሰራተኛውን በሚከተለው

ኢሜል ያስተላልፉ፡-

[email protected]

12. አዳዲስ ነገሮች

ከጊዜ ወደጊዜ ይህንን የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ የመቀየር ወይም የማሻሻል መብታችን የተጠበቀ ነው፡፡

በዚህ የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ ላይ የምናደርጋቸው ማንኛውም አይነት ማሻሻያዎች በዚህ ገፅ እና በድረ-ገፃችን ላይ የሚወጡ

ይሆናል፡፡ እነዚህ ማሻሻያዎች በድረ-ገፃችን ላይ ልክ እንደተለቀቁ ተፈፃሚ የሚሆኑ ሲሆን እርስዎም እንዳነበቧቸው እና

እንደተስማሙባቸው ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡

ስለሆነም ይህን የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ በየጊዜው እየጎበኙ እራስዎን በወቅቱ ካለው የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ ዝርዝር

ሁኔታዎች እና ለውጦች ጋር ማስተዋወቅ ይኖርብዎታል፡፡

13. የጉብኝት አሻራ(ኩኪሶች)

የጉብኝት አሻራዎች(ኩኪስ) የምንላቸው ድረ-ገፁ ወደ እርስዎ የኮምፒውተር የመረጃ ማከማቻ የሚያስተላልፋቸው ጥቃቅን መረጃዎች

ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ የኢንተርኔት የመፈለጊያ መሳሪዎች እነዚህን የጉብኝት አሻራዎች (ኩኪሶች) ወዲያውኑ የሚቀበሏቸው ቢሆን፣

እርስዎ ከፈለጉ ግን የእርስዎን የኢንተርኔት መፈለጊያ መሳሪያ እነዚህን የጉብኝት አሻራዎ እንዳይቀበል ለመከልከል ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን

ይህን ሲያዲርጉ አንዳንድ የድረ-ገፁን አገልግሎቶች ሙሉ ለሙሉ ከመጠቀም ሊገድብዎት ይችላል፡፡ የጉብኝት አሻራዎች(ኩኪስ)

የፈጠራቸው ሰርቨር ብቸኛ ንብረቶች ሲሆኑ በሌሎች ሰርቨሮች ሊከፈቱ/ሊታዩ አይችሉም፡፡ ይህም ማለት እርስዎ በድረ-ገፁ ላይ

የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለመከታተል አላማ ሊውሉ አይችሉም፡፡ ምንም እንኳን እነዚህ የጉብኝት አሻራዎች(ኩኪሶች) የተጠቃሚን

ኮምፒውተር ለመለየት ቢያስችሉም፣ የተጠቃሚውን ሰው ማንነት እና የይለፍ ቃላት እንዲሁም የባንክ ሒሳብ ማንቀሳቀሻ ካርድን

የሚመለከቱ መረጃዎች በጉብኝት አሻራዎች(ኩኪስ) ውስጥ አይከማቹም፡፡

የጉብኝት አሻራዎችን(ኩኪስ) ለሚከተሉት ግልጋሎቶች ልንጠቀምባቸው እንችላለን፡፡

- ማንነትዎን ለመለየት እንዲሁም የአካውንትዎን መረጃ ለመጠቀም፤

- የተመልካቾቻችንን መጠን፣ ስፋት እና ሁኔታ ለመገመት፣

- የገፁ ጎብኚዎች ተመሳሳይ ማስታወቂያዎችን በምን ያህል ድግግሞሽ እንደሚያዩ ለመቆጣጠር፣

- ምርጫዎችን ለመለየት፣ ገፁን ለማሻሻል እና ወቅታዊ ለማድረግ፣

14. ደህንነት

ከኢንተርኔት ተፈጥሯዊ ባህሪ አንፃር የግል መረጃዎ ሙሉ ለሙሉ እንደሚጠበቁ ለማረጋገጥ አንችልም፡፡ በተጨማሪም ገፁ አገልግሎት

ላይ በሚውልበት ጊዜ የሚፈጠሩ ማንኛውም የህግ መጣሶች ተጠያቂ አንሆንም፡፡

በገፆቻችን ደህንነት ሙሉ ለሙሉ የምንተማመን ከመሆናችንም በላይ በዚህ ዙሪያ ምንም አይነት ችግር እንዳይገጥመን መስራት

ተቀዳሚ ተግባራችን ነው፡፡

ይህ ፖሊሲ ለመጨረሻ ጊዜ የተሻሻለው እ.ኤ.አ በዲሴምበር 8፣ 2015 ነው፡፡__